ለ60 ሚሊየን ዜጎች የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ግንዛቤ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ተሰጥቷል - አቶ ሰለሞን ሶካ፡ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

Verschachtelte Anwendungen

Asset-Herausgeber

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን በይፋ አስጀመሩ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን በይፋ አስጀመሩ Sa, 31 Aug 2024

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ Mi, 21 Aug 2024

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛዉን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ አስጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛዉን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ አስጀመረ Mi, 21 Aug 2024

ኢመደአ የራሱን የህክምና ማዕከል አስመረቀ

ኢመደአ የራሱን የህክምና ማዕከል አስመረቀ Do, 15 Aug 2024

Asset-Herausgeber

null ለ60 ሚሊየን ዜጎች የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ግንዛቤ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ተሰጥቷል - አቶ ሰለሞን ሶካ፡ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር 60 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ግንዛቤ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መሰጠቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ፡፡አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሃገር ሉዓላዊነትበሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 – 30 /2016 . የተካሄደውን 4ኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በስኬት መጠናቀቅ አስመልክቶ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

4ኛው የሳይበር ደህንነት ወር ለማሳካት በእቅድ ከተያዙት አላማዎች መካከል በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የነገዉን ትዉልድ ያተኮሩ የግንዛቤ ስራዎችን ማከናወን ተቋማት ይህን አለማቀፍና ሃገራዊ ሁነት በራሳቸዉ አዉድ ወስደዉ ተቋማዊ ንቅናቄን እንዲያደርጉ መደገፍ፣ የሳይበር ማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ማጎልበት፣ የተቋማት የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት ማሻሻል፣ የሳይበር ደህንነት ጥናትና ምርምሮችን ማበረታታት፣ እንዲሁም በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ መስክ የተሰማሩትን የግሉን ዘርፍ ማነቃቃት እንደበነር አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡

4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከተነሳለት አላማ አኳያ የሳይበር ማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ለማጎልበት የሚያስችሉ ከወትሮ የተለዩ ስልቶችን በማካተት በአዝናኝና አስተማሪ ፊልምሥውር ውጊያፊልም በመጀመር እንዲሁም ጥናትና ምርምር ላይ መሰረት ያደረጉ ተጨባጭ ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ቁመናን የፈተሹና ቀጣይ ትልማችንን የነደፍንበትና ተቋማትን በሰፊዉ ያሳተፈ ነበር ሲሉ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም እንደገለጹት በዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር በተካሄዱ ኮንፈረንሶችና የአዉደ ርዕይ መርሃ ግብሮች 150 በላይ ተቋማት የተዉጣጡ ከአምስት (5,000) በላይ ሰዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አራት ዋና ዋና መርሃ ግብሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ የወሩ የመክፈቻ መርሃ ግብር የነበረውና በኢመደአ ተዘጋጅቶ ለሕዝብ እይታ የበቃውሥውር ውጊያየተሰኘ ፊልም፤ በሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር የቀረበው ሃገራዊ የሳይበር ስጋት ተጋላጭነት፤ በሦስተኛ ሳምንት ይፋ የተደረገውሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃየጥናት ውጤት፣ እንዲሁም በሃገራዊ የሳይበር ደህንነት የሕግ ማዕቀፍ፣ ፖሊሲና ስታንዳርድ ዙሪያ ለክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና የአይ.. ቢሮ ሃላፊዎች በቪዲዮ ኮንፍረንስ የተሰጠ የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ፤ በአራተኛውና በወሩ የመጨረሻ መርሃ ግብር የተካሄደሃገራዊ የሳይበር ደህንነት የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስበወሩ የተካሄዱ ዋና ዋና መርሃ ግብሮች መሆናቸውን አቶ ሰለሞን ሶካ አብራርተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በማጠቃለያ መልዕክታቸው 4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን ገልጸው፤ በተለይም ከኢመደአ በተጨማሪ ሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት እንደ አዉዳቸዉ በመዉሰድ የሳይበር ደህንነት ንቅናቄን ማካሄድ እንዳለባቸው እና ይህን ተግባራዊ ያደረጉ ተቋማት መታየታቸዉ ከፍተኛ ተስፋ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም 4ኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ስፖንሰር በማድረግ፣ በአዉደ ርዕይ አቅራቢነት፣ በተሳታፊነት፣ በአወያይነት፣ በጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢነት፣ በሚድያ ስርጭት፣ በአዘጋጅነትና በሌሎችም በማንኛዉም ረገድ 4ኛውን የሳይበር ደህንነት ወር  ስኬታማ ለማድረግ አስተዋጽዖ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።