የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Verschachtelte Anwendungen

Asset-Herausgeber

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ Mi, 27 Nov 2024

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ጋር ተወያዩ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ጋር ተወያዩ Mo, 25 Nov 2024

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል ዙሪያ 30 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመርቋል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል ዙሪያ 30 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመርቋል Fr, 22 Nov 2024

“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች ባሻገር አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው የሳይበር ምህዳር ላይም አቅም ለመገንባት እየሠራ ነው” ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የመከላከያ ሚንስትር

“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች ባሻገር አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው የሳይበር ምህዳር ላይም አቅም ለመገንባት እየሠራ ነው” ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የመከላከያ ሚንስትር Fr, 22 Nov 2024

Asset-Herausgeber

null የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች የሥራ አውዳቸውን መሰረት ያደረገ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በሥራ ባሕል ግንባታ፣ በዲጂታል ውቅረ ሃሳብ፣ እና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አስጀምረዋል፡፡

እጅግ ተለዋዋጭ በሆነው የዲጂታል ዓለም ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ለመዝለቅ ጠንካራ የሥራ ባሕል መገንባት እና ዲጅታል ውቅረ ሃሳብ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በጋራ ሆነው መውሰዳቸው ከተሰማሩበት የሥራ አውድ አኳያ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መድረክ እንደሆነ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በስልጠና ማስጀመሪያው ላይ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት በጀርመኑ መኪና አምራች መርሰዲስ ቤንዝ ውስጥ ለረዥም አመታት በተለያዩ የሙያና የሃላፊነት ቦታዎች ላይ እየሰሩ የሚገኙት ዶ/ር ጸጋዬ ደግነህ ናቸው፡፡