የአጭር ፊልም ውድድር አሸናፊዎች ተሸለሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 5ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በማስመልከት ባዘጋጀው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ የአጭር ፊልም ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑት ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

በተካሄደው ውድድር ላይ 1ኛ በመውጣት የሁለት መቶ ሺ ብር (200,000 ብር) አሸናፊ የሆኑት እነ ቢንያም ሰለሞን “ሰማያዊ ሽብር’ በሚል አጭር ፊልም ሲሆን፤ 2ኛ የወጣው ኤልያስ ብርሃኑ “የንስር ዓይኖች” በተሰኘ አጭር ፊልም የመቶ ሺ ብር (100,000 ብር) አሸናፊ ሆኗል፤ በውድድሩ የ3ኛነት ደረጃን የያዘው ሰዒድ አወል “ክሊክ” በሚል አጭር ፊልም የ50,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ለአሸናፊዎች ሽልማት የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ባስተላለፉት መልዕክት የጥበብ ሥራ ሰውን ለማንቃት፣ለማስተማር ሁነኛ መንገድ በመሆኑ እኛን መሰል ተቋማት ይህንን መንገድ በመጠቀም የማሕበረሰቡን የሳይበር ደሕንነት ንቃተ ሕሊና ማጎልበት እና ባሕል መገንባት ላይ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በተካሄደው 4ኛው የሳይበር ደህንነት ወር ላይ “ስውር ውጊያ” በሚል ርእስ አስተዳደሩ ባሰራው አስተማሪ ፊልም የተቋማትንና የማኅበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ለማጎልበት የሚያስችል ውጤት መገኘቱን ያወሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ፤ አምና የነበረውን ተሞክሮ በማስፋት ዘንድሮም በርካታ ወጣቶችን ለማሳተፍ የሚያስችል የአጭር ፊልም ውድድር መዘጋጀቱና ጠቁመዋል፡፡

በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሃኒባል ለማ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት 5ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደሀንነት ወር በማስመልከት አስተዳደራችን ባዘጋጀው የአጭር ፊልም ውድድር ላይ የቀረቡት ፊልሞች “በአስገራሚ ሁኔታ በፊት በፊት ስንናገረው የኛ ጉዳይ ብቻ የሚመስለውን ግን የሁሉ ጉዳይ መሆን ያበትን የሳይበር ደህንነት ፅንሰ ሃሳብ ያሳዩ እና አሁን አሁን ማህበረሰባችን የሳይበር ደህንነት የሰርክ ኑሯችን ላይ ያለ መሆኑን እየተረዳ መመጣቱን ያሳዩበት ነው” ብለዋል፡፡

5ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በማስመልክተ በተዘጋጀው የአጭር ፊልም ውድድር ላይ በቁጥር አርባ ሰባት (47) የሚደርሱ ተሳታፊዎች አጫጭር ቪዲዮዎችን በመስራት በውድድሩ ሲሳተፉ፣ በተቀመጠው 10 መስፈርት (የሰዓት አጠቃቀም፣ የራስ ፈጠራ፣ የምስልና የድምጽ ጥራት፣ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ ወዘተ) ከሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እና ከአርቱ ማኅበረሰብ በተውጣጡ ዳኞች ተገምግመው በመጀመሪያው ዙር 14 ፊልሞች ከተመረጡ በኋላ በድጋሚ ማጣሪያ አምስት የሚሆኑ ፊልሞች ለመጨረሻ ዙር እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡ በዚህም በዛሬው እለት በተካሄደው የ5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአምስቱም ተወዳዳሪዎች ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን፤ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡ ፊልሞች ደግሞ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች