ተቋማቱ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ )፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የስምምነቱ ዓላማ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ለሲቪል ምዝገባ እና ለወሳኝ ኩነት የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ለማልማት፣ ለማማከር፣ ለመተግበር፣ በቀጣይነት ክትትል ለማድረግ እና በትብብር ለመስራት ያለመ ሲሆን እነዚህ አገልግሎቶች ከዲጂታል መታወቂያ ጋር የተሳሰሩ እንደሆነ በመግባቢያ ስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግሰት ሃሚድ እንደገለጹት የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሰራሩን አውቶሜት ለማድረግ ያሳየውን ቀርጠኝነት አድንቀው፤ ኢመደአ የኤጀንሲውን አሰራር ዲጂታላይዝ በማድረግ ሂደት ላይ ለመደገፍ እና በማማከር ረገድ ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰራ ተናግረዋል። በተለይም የሲቪል ምዝገባ፣ የወሳኝ ኩነቶች ስታትስቲክስ እና የነዋሪዎች መታወቂያ (CRVS with Residents ID) ሲስተም የቴክኖሎጂ መፍትሄ ልማት እና ትግበራ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ ቀጣይነት ያለው ክትትል፣ ድጋፍ እና የማማከር ሥራዎች እንደሚሰሩ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸዉ አዲስ የሚገነባው የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ስርዓት ከተማዋን ስማርት ለማድረግ እና በከተማዋ ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል የመግባቢያ ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ አኳያ ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊውን የማማከር ሥራ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሲቪል ምዝገባ፣ የወሳኝ ኩነቶች ስታትስቲክስ እና የነዋሪዎች መታወቂያ (CRVS with Residents ID) ሲስተም በአጭር ጊዜ ውስጥ በማልማት ለአገልግሎት ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የሲቪል ምዝገባ፣ የወሳኝ ኩነቶች ስታትስቲክስ እና የነዋሪዎች መታወቂያ ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር መተሳሰሩ በቀጣይ በቅንጅት ለመስራት አስቻይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የዜጎችን መሰረታዊ የመታወቅ መብት ለማረጋገጥ እንዲሁም መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነቱ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ገልጸዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ በመገኘት ከአራቱ ተቋማት ጋር የተፈራረሙት የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው እንደገለጹት ኤጀንሲው በዋናነት የሚያከናውናቸው ተግባራት የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪነት መታወቂያ ሲሆን፤ ቀደም ባለው አሰራር ዘመኑን የሚዋጅ ባለመሆኑን የኤጀንሲውን አስረራር ዲጂታላይዝ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የመግባቢ ስምምነቱ የኤጀንሲውን አስራር በማዘመን ለዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች