በአስተዳደሩ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እና በመንግስት የመቶ ቀናት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እና በመንግስት የመቶ ቀናት ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በውይይት መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገር አቀፍ ደረጃ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ በተቋም ደረጃ ውይይት መደረጉ እንደ ሀገር እየተሰሩ በሚገኙ የልማት ሥራዎች ላይ የተሟላ ግንዛቤ ለመያዝ ያስችላል ብለዋል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚው የመቶ ቀናት አፈጻጸም በጥቅሉ እንደ ተቋም የእኔ ድርሻ የት ነው የሚለውን ወስደን የድርሻችንን እንድናበረክት ዕድል የሰጠ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከዚህ አኳያ የአስተዳደሩ አመራርና አባላት ሀገራዊ የልማት ሥራዎችን በአግባቡ በመገንዘብ ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የመቶ ቀናት ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሪፖርት በኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ የቀረበ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የፀጥታ ጉዳይን ጨምሮ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆናም በአብዛኞቹ ዘርፎች ተስፋ ሰጭ የኢኮኖሚ ዕድገት እያሳየች መሆኗ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ በመቶ ቀናቱ አጠቃላይ የ8 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በዚህም በሩብ ዓመቱ በበርካታ ቁልፍ የትኩረት መስኮች አስተዳደሩ አመርቂ የሚባል አፈጻጸም ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ በተለይም በዓለም አቀፉ የሳይበር ደህንነት አመላካች የደረጃ ሰንጠረዥ (Global Cyber Security Index) እንደሀገር ከፍተኛ መሻሻል ማስመዝገብ መቻሉ በዘርፉ ወሳኝ ሥራዎች መሠራታቸውን የሚያመላክትና በትልቅ ስኬትነት ሊወሰድ የሚገባ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ከአራት አመታት በፊት እ.ኤ.አ 2020 በዓለም አቀፉ የሳይበር ደህንነት አመላካች ደረጃ እንደ ሀገር የነበረን ውጤት 20 ከመቶ የነበረ ሲሆን በ2024 እ.ኤ.አ ወደ 76 በመቶ ከፍ ማለት መቻሉን በሪፖርቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት 2,556 (ሁለት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ስድት) የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን መከላከል መቻሉን ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም በውይይቱ በሁለቱም አጀንዳዎች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የ

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች