ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርሞች

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

* ሲርኩኒ

* ደቦ

* ኤርጋ

ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂና የእውቀት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ቁልፍ መፍትሔ ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር በተለያዩ የቴክኖሎጂ አቅሞች ላይ፤ በተለይም ክልከላ ባለባቸው የቴክኖሎጂ አቅሞች ላይ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል።

አስተዳደሩ ባለቤትነትን ካረጋገጠባቸው የቴክኖሎጂ አቅሞች መካከል ደህንነታቸው የተረጋገጠ የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርሞች በዋናነት ይጠቀሳሉ።

* ሲርኩኒ (Sirkuni):- ይህ የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርም ልክ እንደሌሎች የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርሞ (ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም ወ.ዘ.ተ) የድምጽ፣ የጽሁፍ፣ እና የቪዲዮ መልእክቶችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ሙሉ በሙሉ በኢመደአ አቅም የተሰራ እና ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ነው።

* ደቦ (Debo):- ይህ የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርም የቪዲዮ ኮንፍረንስ ለማከናወን የሚያስችል ሲሆን፤ ይህም በተመሳሳይ ሙሉ በሙሉ በኢመደአ አቅም የተሰራ እና ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ነው።

* ኤርጋ (Erga):- የኢ-ሜይል አገልግሎት የሚሰጡንን እንደ ጂ-ሜይል፣ ያሁ ወ.ዘ.ተ የሚተካ በኢመደአ አቅም የበለጸገና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የኢ-ሜይል አገልግሎት ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማሳካት፤ በአንድ በኩል የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ተልእኮውን እየተወጣ ሲሆን፤ በሌላም በኩል አስቻይ የሆኑ የቴክኖሎጂ አቋሞችን በማልማት ሀገራዊ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል።

ከላይ የቀረቡትን የቴክኖሎጂ ምርቶች ጨምሮ ሌሎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምርትና አገልግሎቶችን በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው እንዲጎበኙ እንጋብዝዎታለን።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን ጥር 19/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መከፈቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ እና ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ።

Publicador de contenidos


የቅርብ ዜናዎች