ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ለኢመደአ፣ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት  አመራሮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ስልጠናውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በይፋ አስጀምረውታል፡፡ እንደ ሀገር ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ለመቆጣጠር መንግስት በየደረጃውና በየዘርፉ ጠንካራ ትግል ከማካሄድ ባለፈ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ውጤታማ  የአሰራር ስርአት እንዲዘረጋ አቅጣጫ ማስቀመጡን የገለጹት አቶ ዳንኤል፤ ከዚህ አኳያ እንደ ቴክኖሎጂ ተቋም ይህን እውን ለማድረግ ያለን ሚናና ሃላፊነት ወሳኝ በመሆኑ ሃላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።