"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በኢመደአ ተከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራርና አባላት "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን (March-8) አከበሩ።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሰው ልጆች ለእኩልነት እና ለፍትሕ ያደረጉት ትግል ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዓል መከበር መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። ቀጣነት ያለውና ዘላቂ ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተቋም ደረጃ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር ዋና ዓላማው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሴቶችን በበቂ ሁኔታ ተሳታፊ ብሎም መሪ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታሳቢ በማድረግ ነው ሲሉም ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በኢመደአ ውስጥ ከባለሙያነት ጀምሮ እስከ ዋና ዳይሬክተር ደረጃ ድረስ ያለፉበትን የሕይወት ተሞክሯቸውን ለበዓሉ ታዳሚዎች አካፍለዋል፡፡ “ሴቶች በሁሉም ነገር ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ተረድተው ከሰሩ በየትኛውም ዘርፍ ስኬታማ ከመሆን የሚያግዳቸው አንዳች ነገር የለም”” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

በሌላም በኩል በበዓሉ ላይ ተገኝተው የሕይወት ተሞክሯቸውን ያካፈሉት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኮምፒዩቲንግ እና አናሊቲክ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰብለ ኃይሉ እና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የናቹራል ላንጉጅ ፕሮሰሲንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮዛ ፀጋዬ እንደተናገሩት፤ ሴቶች በየትኛውም የሙያ መስክ ተሰማርተው ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ የእነሱ ሕይወት ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም ሴቶች የትኛውም አይነት ተግዳሮቶ ሳይበግራቸው በየትኛውም መስክ ብቁ ባለሙያ ከመሆን ባለፈ የመሪነት ሚናን መጫወት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዉ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በበኩላቸዉ ሴቶች የሚፈልጉበት ቦታ ለመድረስ ምንም የሚያዳግታቸዉ ነገር እንደሌለ አንስተዉ ለግባቸዉ ስኬት የወንዶች ድጋፍና ተሳትፎ የማይተካ ሚና እንዳለዉ ጠቁመዋል።

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች