የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ተፈረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፣ አሃዱ ባንክ እና ገዳ ባንክ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት ግብር ከፋዮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያለማውን “ደራሽ” የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት በመጠቀም ባሉበት ሆነው ግብራቸውን ለማሳወቅና ለመክፈል የሚያስችላቸው ነው፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢመደአ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር እንደ ሀገር አቅም ባልተፈጠረባቸው የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ በመግባት ሀገራዊ አቅምን የመገንባት ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የሀገሪቱን የዲጂታል የፋይናንስ ስርአት ከማሳደግ አኳያ የቀደምትነት ሚናን በመውሰድ ከ10 አመት በፊት “ደራሽ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት በማልማት ወደሥራ ማስገባቱን አንስተዋል፡፡ ይህ ሲስተም ባለፉት አስር አመታት ሀገራዊ የዲጂታል የፋይናንስ ስርአት ከማሳለጥ አኳያ ከፍተኛ ሚናን መጫወቱን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በበኩላቸው በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት፤ የኤሌክትሮኒክ የታክስ ክፍያ ስርአት ለግብር ከፋዩ የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና የመንግስትን ወጪ ከሀገር ውስጥ ከሚሰበሰብ ግብር ለመሸፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር በሀገራችን ከሚገኙ ሃያ ሁለት (22) ባንኮች ጋር የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሞ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ በዛሬው እለት አሃዱ ባንክ እና ገዳ ባንክ የኤሌክትሮኒክስ የታክስ ስርአት የሚፈልገውን የሲስተም ዝግጅት በማሟላት ወደ “ደራሽ” የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሃዱ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ሲሳይ ገብሩ፤ እንዲሁም የገዳ ባንክ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ ደሬሳ በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የኤሌክትሮኒክስ የታክስ ስርአት የሚፈልገውን የሲስተም ዝግጅት በማሟላት ወደ “ደራሽ” የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት ውስጥ መግባት መቻላቸው ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች