የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተቋሙ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያለማቸውን ምርት እና አገልግሎቶችን እንዲሁም በተለያዩ የሳይበር ደህንነት ዘርፎች እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ለክቡር አምባሳደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር በተለያዩ የልማት ዘርፎች እያከናወናቸው የሚገኘውን ጠንካራ የትብብር ስራዎችን በሳይበር ደህንነት ዘርፍም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያሰፈልግ ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር ቸን ሃይ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ የሀገሪቷን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እድገት ከመደገፍ አንፃር እየሰራቸው ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት በሌሎች የልማት ዘርፎች ያላቸውን ጠንካራ ትብብር በሳይበር ደህንነት ዙሪያም በመድገም የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለበቸው ገልፀው ለዚህም ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች