የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር/ኢመደአ/ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስረከበ፡፡
ድረ-ገጹ መንግሥታዊ መረጃን በፍጥነት፣ በጊዜ ተገቢነትና ኀላፊነት በተሞላበት መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል እንዲሁም አሁን ያለውን የዲጂታል ዓለም የመረጃ ፍጥነት ያገናዘበ የመንግሥት የመረጃ ፍሰትን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነዉ፡፡
ድረ-ገጹ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አቅጣጫዎችን የሚከተሉ፣ መንግሥትና ሕዝብን የሚያቀራርቡ፣ የሕዝቡን ፍላጎት ለመንግሥት የሚያሳዩ፣ የመንግሥትንም ፍላጎትና ተነሣሽነት ወደ ሕዝቡ የሚያወርዱ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መሠረተ ልማቶችን አስተሳስሮ የያዘ የመረጃ መለዋወጫ ሥርዓት ነው፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ያለማው ድረ-ገጹ ዜጎች በተለያዩ የመንግሥት እና የክልል የቋማት ላይ ያላቸውን ጥያቄ፣ አስተያየት እና ቅሬታ የሚያቀርቡበትን ስርዓት በዉስጡ የያዘ ነዉ።
ድረ-ገጹን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አረያስላሴ ለመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አስረክበዋል።