የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን በይፋ አስጀመሩ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን በይፋ አስጀመሩ sam., 31 août 2024

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ mer., 21 août 2024

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛዉን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ አስጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛዉን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ አስጀመረ mer., 21 août 2024

ኢመደአ የራሱን የህክምና ማዕከል አስመረቀ

ኢመደአ የራሱን የህክምና ማዕከል አስመረቀ jeu., 15 août 2024

Agrégateur de contenus

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑት ታላል አል አዘሪ ጋር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱም የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለዉ ስራ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆናቸዉን የጠቀሱት ታላል አል አዘሪ ይህ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት መስፋት የሚገባዉ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ከኢመደአ ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በይበልጥ በታዳጊዎች የሳይበር ታለንት ልማት ላይ በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳለዉ ሚስተር ታላል ገልጸዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነት እንዲሁም በሳይበር ታለንት ልማት ያካበተውን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ሶካ ከታላል አል አዘሪ ጋር ካደረጉት ውውይት ባሻገር ኢመደአ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፤ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡