የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን በይፋ አስጀመሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገነባውን ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት (National Public Key Infrastructure - PKI) በይፋ አስጀመሩ፡፡   

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ሲቋቋም ዋና ዓላማው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ከዚህ አኳያ የብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት ግንባታ ኢመደአ የተቋቋመበትን ዓላማ ከማሳካት አኳያ ያለው ፋይዳ ጉልህ ነው ብለዋል፡፡

የሀገር ሉአላዊነትን በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ የሳይበር ደህንነታችንን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት አስቻይ የሆነ ሚናን የሚጫወት እና ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን  ሽግግር የጀርባ አጥነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ከብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት በተጨማሪ በቅርቡ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣ እንዲሁም ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እንደ ሀገር ወደ ወደ ምናባዊው ዓለም (Virtual World) በተሟላ መልኩ በመቀላቀል ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የመንግስትና የንግድ ተቋማት የሚያደርጓቸውን የመረጃ ልውውጦች ከደህንነት ስጋት ነጻ እና ህጋዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸው በማድረግ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት (National Public Key Infrastructure - PKI) በይነ-መረብን (Internet) መሰረት ያደረጉ ግንኙነቶችን ደህንነት ተአማኒነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑትን ዲጂታል ሰርተፍኬት በመስጠት፤ የመንግስት ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች፣ እና ግለሰቦች መረጃዎቻቸው ከጠለፋ እና ከማጭበርበር የተጠበቁ መሆናቸውን አውቀው ዲጂታል እንቅስቃሴያቸውን በልበ ሙሉነት እንዲያከናውኑ እንደሚያስችላቸው ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። አያይዘውም ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት የቴክኖሎጂ አቅማችንን ከማሳደግ በላይ፥ እርስ በርስ በተገናኘው አለም ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ተአማኒነትን እና ተጠያቂነት ለማስፈን የሚያስችል ነው ብለዋል።

በብሔራዊ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች ከፍተኛ የመግስት የሥራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ የመሰረተ ልማቱን አገልግሎት ጎብኝተዋል፡፡

Agrégateur de contenus


የቅርብ ዜናዎች