ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ተፈረመ

የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ተፈረመ Sze, 2 júl. 2025

የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ተቀባይነት በማግኘት እውቅና ተሰጠው

የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ተቀባይነት በማግኘት እውቅና ተሰጠው Sze, 25 jún. 2025

የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኢመደአን የዲጂታል ፎረንሲክና የሳይበር ወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎበኙ

የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኢመደአን የዲጂታል ፎረንሲክና የሳይበር ወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎበኙ P, 20 jún. 2025

“ቤተሰብ የሀገር መሠረት” - የኢመደአ የቤተሰብ ቀን በድምቀት ተከበር

“ቤተሰብ የሀገር መሠረት” - የኢመደአ የቤተሰብ ቀን በድምቀት ተከበር Cs, 19 jún. 2025

Tartalom megjelenítő

null ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገለጹ።

ይህን ያሉት ኢትዮጵያ በብራዚል መዲና ብራዚሊያ በተካሄደው የብሪክስ የሳይበር ደህንነት እና ጥበቃ ስብሰባ ላይ በተሳተፈችበት መድረክ ላይ ነዉ።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ምህዳር ለመፍጠር ሀገር አቀፍ ትብብር እና ዓለም አቀፍ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በስብሰባው ላይ ስለ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ገለጻ አድርገዋል።

ፖሊሲው የመንግስት፣ ህዝብ እና የበርካታ ባለድርሻ አካላት የጋራ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ፣ ለቁልፍ የመረጃ መሰረተ ልማቶች እና ለግል መረጃ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም ለዲጂታል የኢኮኖሚ ተግባራት ደህንነቱ የጠበቀ አሰራርን መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነት እንዲጠናከር ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

በብሪክስ ማዕቀፍ አማካኝነት በኢንፎርሜሽን ደህንነት ዘርፍ እድሎችን መጠቀም እና ስጋቶች በጋራ መከላከል እንደሚገባም ነው አምባሳደሩ ያሳሰቡት።

ስብሰባው የብሪክስ አባል ሀገራት የአይሲቲ ደህንነት ይዞ የመጣቸው እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ሀሳቦችን እንዲለዋወጡ እና ሀገራዊ ተሞክሯቸውን እንዲያቀርቡ ምቹ አጋጣሚን መፍጠሩ ተመላክቷል።

አባል ሀገራቱ በጉዳዩ ላይ ብሪክስ ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተመላክቷል።