የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2016 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ Sze, 7 máj. 2025

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ P, 25 ápr. 2025

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ P, 25 ápr. 2025

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ H, 14 ápr. 2025

Tartalom megjelenítő

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2016 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለተቋሙ ማህበረሰብ እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የ2016 አዲስ አመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአዲስ ዓመት መልዕክታቸዉ፤ ያለፈዉ 2015 ዓመት በስኬትና በተግዳሮት የታጀበ ነበር ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከስኬቶቻችን መካከል በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የነበረዉ ጦርነት በእርቅ የተቋጨበት፣ የአራተኛዉ ዙር የታላቁ የህዳሴ ግድብ የዉሃ ሙሌት በስኬት የተጠናቀቀበት፣ አገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመፍጠንና በመፍጠር እሳቤ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የይቻላል መንፈስ የተፈጠረበት ዓመት እንደነበር ገልጸዋል።

በተቋም ደረጃ በ2015 ዓ.ም በለዉጥ ዉስጥ ከፍተኛ የሚባሉ ስራዎች መሰራታቸዉን ያወሱት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን በተገባደደዉ ዓመት በይፋዊ የህዝብ መሰረተ ልማት/PKI ግንባታ ፣ በአገራችን በሳይበር ጥቃት ሊደርስ የነበርን ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለዉን ኪሳራ በማስቀረት ረገድ ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሀይል እጥረት ለመቅረፍና የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ባለ ልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን በማሰልጠንና በማስመረቅ ደረጃ ስኬታማ ዓመት እንደነበር ገልጸዋል።

በሌላ መልኩ አገራችን ባገባደድነው 2015 ዓ.ም በብዙ መልኩ በዉስጥም በዉጭም የተፈተነችበት ዓመት መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ ጠላቶቻችን የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በአይነትና በስፋት በመጨመር እንዲሁም የዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ከፍተኛ የሚባል የስነልቦና ጦርነት የከፈቱበት ዓመት እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የገጠሙንን ተግዳሮቶች እንደ አገር ችግሮችን የማለፍ እሴቶቻችንን በመጠቀም፣ ከሌሎች የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን አገራችን እንድትጸና የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ሰለሞን በተቋም ደረጃ የገጠሙንን ችግሮች ደግሞ በጥብቅ ዲስፕሊን፣ በሙያዊ ልህቀትና የአገር ፍቅር ስሜት እየተሻገርን እዚህ ደርሰናል ብለዋል።

ኢመደአ በአዲሱ ዓመት አገራዊ ፋይዳቸው ላቅ ያሉ ተግባራት ማለትም የሳይበር ሉዓላዊነት በሚያስጠብቁ ዘርፎች፣ የቴክኖሎጂ ባለቤትነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ አገራዊ ልማትን የመደገፍ፣ የአገረ መንግስት ግንባታ ሂደትን የማሳለጥና ኢትዮጵያን የማጽናት ስራ ላይ ተቋማዊ ሃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

በአዲሱ ዓመት መላው ኢትዮጵያውያን ቀድሞ የነበረንን የመረዳዳትና የመተዛዘን ባህል በማስቀጠል ለተቸገሩና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለንን በማካፈል በዓሉን በአንድነት፣ በደስታና በፍቅር ማክበር እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም መጪው 2016 አዲስ ዓመት ለኢመደአ ማህበረሰብ እና ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን የሰላም ፣የፍቅር ፣ የብልፅግና የመተሳሰብ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።