የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነትን መጠበቅ የሀገር ደኅንነትና ሉዓላዊነትን መጠበቅ ነው

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነትን መጠበቅ የሀገር ደኅንነትና ሉዓላዊነትን መጠበቅ ነው V, 13 okt. 2024

“የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

“የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ V, 13 okt. 2024

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ኃላፊነት ነው

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ኃላፊነት ነው V, 13 okt. 2024

ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የቁልፍ መሰረተ ልማቶቻችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው

ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የቁልፍ መሰረተ ልማቶቻችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው V, 13 okt. 2024

Tartalom megjelenítő

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑት ታላል አል አዘሪ ጋር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱም የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለዉ ስራ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆናቸዉን የጠቀሱት ታላል አል አዘሪ ይህ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት መስፋት የሚገባዉ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ከኢመደአ ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በይበልጥ በታዳጊዎች የሳይበር ታለንት ልማት ላይ በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳለዉ ሚስተር ታላል ገልጸዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነት እንዲሁም በሳይበር ታለንት ልማት ያካበተውን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ሶካ ከታላል አል አዘሪ ጋር ካደረጉት ውውይት ባሻገር ኢመደአ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፤ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡