ID4Africa2025 ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
Tartalom megjelenítő
ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በይፋ የተከፈተውን #ID4Africa2025 በማስተናገዷ፣ #ኢትዮጵያ ኩራት ይሰማታል። ID4Africa ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ልማትን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ሰብአዊ ጥረቶችን የሚያበረታቱ ጠንካራ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የማንነት ዐውዶችን በመገንባት፣ የአፍሪካ ሀገራትን ለመደገፍ ቁርጠኛ የሆነ የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ከተበታተነው የመታወቂያ ሥርዓት አልፋ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ወደተጀመረው አስተማማኝ፣ ሁሉንም ያካተተ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መሸጋገሯን አጽንዖት ሰጥተዋል። ለፋይዳ እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል። 90 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡ ፋይዳ ሁሉም ዜጎች - በተለይ ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
እንደ ፋይናንስ፣ ጤና እና ትምህርት ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የተቀናጀው ፋይዳ፣ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር እያገዘ መሆኑንም ገልጸዋል።