ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI)

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ ይዟቸው ከቀረቡት ምርትና አገልግሎቶች መካከል አንዱ ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI) ነው።

ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት በዲጂታል ዓለም ውስጥ መተማመንን እና ደህንነትን የሚያረጋግጥ መሠረተ ልማት ሲሆን፤ የህግ ማዕቀፎች፤ የአሰራር ስርአቶች፤ መተግበሪያዎችን (Softwares) እንዲሁም መሥሪያ መሰረተ ልማቶችን በቅንጅት በመጠቀም የአሲሜትሪክ ክሪፕቶ ስርአትን የምናስተዳድርበት ስርአት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ የይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት ዳታ ማዕከል (Data Center) ገንብቶ በማጠናቀቅ ብሔራዊ የሩት ሠርተፊኬት ባለስልጣን (National Root CA) አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።

ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት ለኤሌክትሮኒክ የመንግስት አገልግሎቶች፣ ለባንክና ፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለቴሌኮሚዩኒኬሽን ወ.ዘ.ተ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን ጥር 19/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መከፈቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ እና ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ።

Tartalom megjelenítő


የቅርብ ዜናዎች