ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ አተገባበርን በሚመለከት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር የትኩረት አቅጣጫ በሆነው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

ባሳለፍነው 2016 በጀት አመት ሰኔ ወር ላይ በሚንስትሮች ምክር ቤት በጸደቀውና ሥራ ላይ እንዲውል በተወሰነው የተሻሻለው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ በምን መንገድ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት በሚያመላክቱ ነጥቦች ላይ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ከሚያስተዳድሩ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲውን ወደተግባር ለማስገባት ምን ይደረግ የሚሉ ጉዳዮች በተሳታፊዎች ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ፖሊሲውን ለማስተግበር የሚያስችሉ ዝርዝር ህጎች ማለትም አዋጆች፣ ደንብና መመሪያዎች ማዘጋጀት ቀዳሚው መሆኑ ተነስቷል፡፡

ተቋማት የየራሳቸውን የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና የሕግና የአሠራር ሥርዓት ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ ትብብር ማጠናከር፤ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በበቂ ሁኔታ ማፍራት፤ እንዲሁም ከላይ ወደታች የሚዘረጋ፣ ወጥ የሆነና ማዕከላዊ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት ፖሊሲውን ለመተግበር መሠረታዊ ጉዳዮች መሆናቸው በተሳታፊዎች ተለይተው ቀርበዋል፡፡ ሚንስትር መስሪያ ቤቶችና ሌሎችም ተቋማት የሳይበር ደህንነት ጉዳይን በመዋቅሮቻቸው ውስጥ እንደ አንድ ዋና የሥራ ሂደት አድርገው ማቋቋም እንደሚገባቸውና በዘርፉ ተገቢው የንቃተ ህሊናና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሥራትም ፖሊሲውን ለመተግበር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከውይይቱ በኋላ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ እና የኢንፎርሜሽን አሹራንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀኒባል ለማ ከተሳታፊዎች በቀረቡ ሃሳቦች ላይ የማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲው ከተዘጋጀ በኋላ ዋነኛው ጥያቄ የሆነው እንዴት ይተግበር የሚለው መሆኑን ያመላከቱት አቶ ሀኒባል፤ ለዚህም ዋነኛው መፍትሔ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይቶችን ማካሄድና የትግበራ መርሃ ግብር ቀርጾ ወደሥራ መግባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ ሀገራዊ የሳበር ደህንነት ፖሊሲውን ለመተግበር እንደተግዳሮት ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ የበጀትና የፋይናንስ ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሀኒባል ፖሊሲው ሲዘጋጅም ይህንን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

በተጫማሪም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ጉዳይ ሌላው እንደተግዳሮት የሚነሳ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር መስራትና እስከዚያው ግን በዘርፉ ከሞላ ጎደል ተማሳሳይ ሞያ ካላቸውና በቂ ልምድ ካካበቱ ባለሙያዎች ጋር ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በአጠቃላይ የአቅም ግንባታ ሥራን ጨምሮ፤ ቴክኖሊጂ፣ ሰው እና የአሠራር ሥርዓት ጋር የተገናኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ፖሊሲውን ወደተግባር በማስገባት ውጤቱን ለመለካት በቀጣይም ተጨማሪ ውይይት ማድረግ እንደሚገባና ለዚህም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሩ ክፍት መሆኑን በማመላከት አቶ ሀኒባል ለማ ውይይቱን አጠቃለዋል፡፡