የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Aplicações Aninhadas

Publicador de Conteúdos e Mídias

በኢመደአ እና በማዕድን ሚንስቴር መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

በኢመደአ እና በማዕድን ሚንስቴር መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ Qua, 22 jan 2025

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በፍጥነት ጸድቆ ተግባር ላይ መዋል እንደሚገባ ተገለጸ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በፍጥነት ጸድቆ ተግባር ላይ መዋል እንደሚገባ ተገለጸ Ter, 21 jan 2025

ኢመደአ በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን አስመረቀ

ኢመደአ በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን አስመረቀ Seg, 13 jan 2025

ኢመደአ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ።

ኢመደአ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ። Seg, 13 jan 2025

Publicador de Conteúdos e Mídias

null የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች የሥራ አውዳቸውን መሰረት ያደረገ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በሥራ ባሕል ግንባታ፣ በዲጂታል ውቅረ ሃሳብ፣ እና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አስጀምረዋል፡፡

እጅግ ተለዋዋጭ በሆነው የዲጂታል ዓለም ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ለመዝለቅ ጠንካራ የሥራ ባሕል መገንባት እና ዲጅታል ውቅረ ሃሳብ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በጋራ ሆነው መውሰዳቸው ከተሰማሩበት የሥራ አውድ አኳያ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መድረክ እንደሆነ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በስልጠና ማስጀመሪያው ላይ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት በጀርመኑ መኪና አምራች መርሰዲስ ቤንዝ ውስጥ ለረዥም አመታት በተለያዩ የሙያና የሃላፊነት ቦታዎች ላይ እየሰሩ የሚገኙት ዶ/ር ጸጋዬ ደግነህ ናቸው፡፡