የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች
የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች
* Soc-as-a-Service
* Cyber Security Audit Services
* Security Clearance Services
* Governance Risk and Compliance Services
ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ተቋማት (የመንግስትም ይሁን የግል) ከውስጥም ይሁን ከውጭ የሚቃጣባቸውን የሳይበር ጥቃት ስጋቶች አስቀድሞ ለመከላከል ከተከሰቱም ደግሞ በፍጥነት ማገገም የሚችሉበትን አቅም እንዲገነቡ ማስቻል ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ተቋማት (የመንግስትም ይሁን የግል) ጠንካራ የሳይበር ደህንነት አቅም ለመገንባት የሚያስችላቸውን የተለያዩ የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶችን ይሰጣል።
አስተዳደሩ ከሚሰጣቸው የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በዋናነት ይጠቀሳሉ።
* Soc-as-a-Service (Security Operation Center-as-a-service):- በኢመደአ የሚገኘው Ethio-CERT (Ethiopia's Computer Emergency Response Team) የሀገራችንን ቁልፍ ተቋማት እና መሠረተ ልማቶች ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት ስጋቶች 24/7 የሚጠብቅ ነው። በሌላም በኩል ተቋማት የዲጂታል ሃብቶቻቸውን ከሳይበር ጥቃቶች ለመጠበቅ የሚያስችላቸውን አቅም መገንባት ይጠበቅባቸዋል። ከዚህ አኳያ ኢመደአ ለተለያዩ ተቋማት (የመንግስትም ይሁን የግል) እንደየአውዳቸው ጠንካራና የማይበገር የሳይበር ደህንነት ቁመና እንዲገነቡ የሚያስችላቸውን አገልግሎት (Security Operation Center-as-a-service) ይሰጣል።
* የሳይበር ደህንነት ፍተሻና ግምገማ አገልግሎት (Cyber Security Audit Services):- ይህ የሳይበር ደህንነት አገልግሎት የተቋማትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች፣ ሲስተሞች እንዲሁም አጠቃላይ የሳይበር ደህንነት እንቅስቃሴዎች ስታንዳርዱን መሠረት ያደረገ ፍተሻና ግምገማ በማከናወን ተቋማት ማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችላቸውን አቅም የሚገነባ ነው።
* Security Clearance Services:- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ አስፈላጊውን ቁጥጥር የማድረግና ፍቃድ የመስጠት ነው። ከዚህ አኳያ አስተዳደሩ በሀገር ደህንነት ላይ ስጋት ሊደቅኑ የሚችሉ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ቁጥጥር እና ፍቃድ የመስጠት አገልግሎት ይሰጣል።
* Governance Risk and Compliance Services:- ተቋማት አጠቃላይ የሳይበር ጥቃት ስጋት ለማስተዳደር የሚያስችሏቸውን ተቋማዊ የሕግ ማዕቀፎችን (ፍሬምወርክ፣ ስታንዳርድ ወ.ዘ.ተ) የመቅረጽ፤ እንዲሁም ከሳይበር ደህንነት ስታንዳርዶችና የሕግ ማዕቀፎች አንጻር ያሉበትን ቁመና የመዳሰስና ተጣጣሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አገልግሎት ነው።
ከላይ የቀረቡትን የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች ጨምሮ ሌሎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምርትና አገልግሎቶችን በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው እንዲጎበኙ እንጋብዝዎታለን።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን ጥር 19/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መከፈቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ እና ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ።