ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ከባቢን መገንባት እና የሳይበር ስጋቶችን መከላከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት ወሳኝ እንደሆነ የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን እና ዓውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል ። መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ከባቢን መገንባት እና የሳይበር ስጋቶችን መከላከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የመጨረሻው የትግበራ አመት ላይ እንገኛለን ያሉት ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ በስትራቴጂው የባለፉት የትግበራ ጊዜያት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን በአንጻሩም የተለያዩ ተግዳሮቶች መግጠማቸውን ተናግረዋል። ይህንንም መነሻ በማድረግ የቀጣይ 5 አመታት "የዲጂታል ኢትዮጰያ 2030 ስትራቴጂ" መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በመድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት ወሳኝ የሆኑ ሁለት ረቂቅ ስትራቴጂዎች ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህም: "የዲጂታል መንግስት ስትራቴጂ" እና "የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስትራቴጂ" ናቸው

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች