የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ እና የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ፈርመዋል፡፡

የሥራ ውል ስምምነቱ በዋናነት የኮርፖሬሽኑን የውስጥና የውጭ አሰራር ለማዘመን የሚያስችል የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒነግ ሶፍትዌር ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህም የሰው ሀብት አስተዳደር፤የፋይናንስ አስተዳደር፤ የገበያና ሽያጭ አስተዳደር፤የንብረት አስተዳደር ስርት ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል አስፈላጊውን ሶፍትዌርና ሲስተም በሚፈለገው ጥራት አልምቶ ለማስረከብ ያለመ ነው፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ የአሰራር ስርአትን ዲጂታላይዝ ማድረግ የዘመኑ ጥያቄና ዓለማቀፍ ግንኙነቶችን ለመፈጸም ፈጣንና ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የሥራ ውል ስምምነቱ የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የአሰራር ስርአትን ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ፤ በውሉ መሰረት የኮርፖሬሽኑን የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፐላኒንግ ሶፍትዌር የማበልጸግ ሥራን ከተቀመጠው ቀነገደብ ባጠረና በተሻለ ጥራት ሠርቶ ለማስረከብ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው በበኩላቸው ባስተላለፉት መልክት ከዲጂታል 2030 ግብ መካከል አንዱ በሀገር በቀል ምርት መጠቀም እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ ከማረጋገጥ አኳያ ሀገር በቀል ከሆነው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የሥራ ውል ስምምነት ለማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ልማት አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ተቋማት አንዱና ዋናው በመሆኑ አሰራሩን ዲጂታይዝ በማድረጉ ፈጣን፣ ቀላጣፋና ምርታማነትን የሚጨመር ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ስርአት መገንባት ለተቋሙ ሕልውና መሰረት መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡