የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

Kapslade applikationer

Innehållspublicerare

ኢመደአ በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን አስመረቀ

ኢመደአ በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን አስመረቀ må, 13 jan 2025

ኢመደአ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ።

ኢመደአ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ። må, 13 jan 2025

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ må, 13 jan 2025

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገነባውን አዲስ ዌብ ፖርታል አስረከበ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገነባውን አዲስ ዌብ ፖርታል አስረከበ må, 13 jan 2025

Innehållspublicerare

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው መዝጊያ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር  አቶ ዳንኤል ጉታ ባስተላለፋት መልዕክት የሳይበር ምህዳር አንድ ተጨማሪ የዲፕሎማሲው የመንቀሳቀሻ ምህዳር በመሆኑ የሳይበር ዲፕሎማሲ አቅም መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው የመንግስት ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን በሳይበር ዲፕሎማሲው ዘርፍ ለአራት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው ስልጠና የሳይበር ምህዳሩን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት እንዳገኛችሁ እምነት አለኝ ብለዋል።

በሳይበር ዲፕሎማሲ ዘርፍ የምንሰራቸው የተለያዩ ስራዎች የሀገራችንን ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን የሳይበር ጥቃት እንዳይደርስባቸው የራሱ የሆነ ትልቅ አስተዋፆ እንደሚጫወት የገለጹት አቶ ዳንኤል፤ከአለምአቀፍ አጋሮቻችን ጋር በመሆን የጋራ የሳይበር መከላከያዎችን ማጎልበት እና ለሳይበር አደጋዎች የበለጠ ውጤታማ ምላሽ መስጠት ያስችለናል  ብለዋል     

የዲጂታል መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በየጊዜው እየተሻሻለ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በዘርፉ  ሊኖር የሚገባ እውቀት እና ችሎታዎችም እንዲሁ ሊጎለብት እንደሚገባ አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡ በየጊዜው ከሚለዋወጡት የሳይበር አደጋዎች እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር ለመራመድ ስልቶቻችንን በማስተካከል ቀጣይነት ያለው ስልጠና እንደሚያስፈልግ ሃላፊዉ ጠቁመዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በብቃት እንደሚጠቀሙበት ያላቸውን  እምነት የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህን በማድረጋችን ለሀገራችን እና ለዜጎቻችን ደህንነት እና ብልጽግናን በማረጋገጥ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የበለጸገ ዲጂታል አለም እንዲኖር በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም /ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናውን በማዘጋጀት ለተሳተፉት ሁሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ መልእክታቸውን  አጠቃለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ ይህ ስልጠና የሰልጣኞችን አቅም ከፍ ከማድረግ ባለፈ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉን ትብብር ወደ ላቅ ደረጃ እንደሚያሳድገዉ እምነቴ ነዉ ብለዋል።