የኢመደአ አመራርና ሰራተኞች ባለፉት የለውጥ አመታት በተመዘገቡ ስኬቶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራሮችና ሰራተኞች ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በሀገራችን በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት እንደሀገር ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት የተገኙ ድሎችን አስመልክቶ “የመጋቢታዊያን የለዉጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ባሳለፍናቸው ሰባት የለውጥ ዓመታት ያስመዘገብናቸውን ድሎቻችንን ለመዘከር እንዲሁም የተሻገርናቸውን ፈተናዎች እና የተገኙ ድሎችን የበለጠ አጉልተን ለማየት የውይይት መድረኩ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ወ/ሮ አስቴር ተናግረዋል።

በለውጡ ማግስት በጸጥታና ደህንነት ተቋማት በተደረገው የሪፎርም ሥራ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅና ሕልውናችንን በማረጋገጥ ረገድ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡ እንደ ተቋም ኢመደአ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን በመስራት የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉንም ተጠቁሟል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ተቋም ካሳካቸዉ ተግባራት መካከል በተለይ ሀገር በቀል የሆኑ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተሰራዉ ስራ የማይተካ ሚና መጫወቱን ወ/ሮ አስቴር ገልጸዋል። በተለይ ሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስቻይ የሆኑ እንደ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI)፣ የዳታ ማዕከል ግንባታ፣ ሀገር በቀል የኮሚዩኒኬሽን መተግበሪያዎች በማሳያነት ተነስተዋል።

የሳይበር ደህንነት የሕግ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት አኳያም ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ጸድቆ ተግባር ላይ መዋሉ ሌላው በስኬት ሊነሳ የሚችል እንደሆነም ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ከመድረኩ የተነሱ ሲሆን የተጀመረውን ለውጥ በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና የሀገራችንን ሁለንተናዊ ልማት ዕውን ለማድረግ እንደ ተቋም የሚጠበቅብንን ሚናና ሃላፊነት ለመወጣት ሁሌም ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲሉ የአስተዳደሩ አመራርና አባላት ገልጸዋል፡፡

Innehållspublicerare


የቅርብ ዜናዎች