ኢመደአ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የጸረ-ኤድስ እና የአፍሪካ ወጣቶች ቀንን አክብሮ ዋለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) የፀረ -ጾታዊ ጥቃት ፣ የአካል ጉዳተኞች፣ ዓለም አቀፍ የጸረ-ኤድስ እና የአፍሪካ ወጣቶች ቀንን አክብሮ ዋለ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አስቴር ዳዊት አራቱም ቀናት በርካታ ተያያዥና የጋራ የሆኑ ጉዳዮች የሚነሱባቸው በመሆናቸው ከተናጠል ይልቅ በጋራ መከበራቸው የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጾታዊ ጥቃት በራሱ ዋነኛው የኤች.ኤ.ቪ ኤድስ መስፋፊያ ፤ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መጨመርና መስፋፋት ደግሞ በዋነኝነት ሴቶችንና ወጣቶችን ተጎጂ እንደሚያደርግ፤ አካል ጉዳተኛ ዜጎች ደግሞ በሁለቱም ምክንያት የበለጠ ለአደጋና ለጉዳት የተጋለጡ በመሆናቸው አራቱንም ጉዳዮች አስተሳስሮ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

“እንደ ተቋም ሁሉንም ቀናቶች ይመለከቱናል ያሉት ወ/ሮ አስቴር ቀናቶችን ማክበራችን ተገቢና ፋይዳውም የጎላ ነው” ብለዋል።

ከዚህ አኳያ ኢመደአ በተለይም እንደ ቴክኖሎጂ ተቋም አካል ጉዳተኞች ታሳቢ ያደረጉ ጥናትና ምርምሮች በማድረግ በቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚታገዙበትና ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ በመንደፍ ሀገራዊ ሃላፊነት ይወጣል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ በበይነ መረብ ስለሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች፣ ስለሚያስከትሉት ጉዳቶች እና የመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

Innehållspublicerare


የቅርብ ዜናዎች