Asset Publisher

null ኢመደአ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ በሚችሉበት ጉዳይ ላይ ስምምነት ተፈረራመ

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ በአስተዳደሩ እና በተቋማቱ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት ስጋትን የመከላከል እና አደጋ መቋቋም የሚስችል የመረጃ ልውውጥ እና ትብብርን ማዕከል ያደረገ ነው።

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ሀገራችን በህገ ወጥ ንግድ ከፍተኛ ገቢ ታጣለች ብለዋል። ይህን ኪሳራ ለመቀነስ አንዱ አቅም ስርአቱን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሂደት በተጓዳኝ የሚመጣውን የሳይበር ደህንነት ስጋት ለመቀነስ ኢመደአ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በሳይበር ስነ ምህዳሩ ላይ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ከመከላከልና ከመጠበቅ አንፃርም አስተዳደሩ ሃላፊነት ወስዶ ይሰራል ብለዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የተከበሩ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ባለፉት አመታት የተከሰቱ ወንጀሎችን ከመከላከል አንፃር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ስራ ሲሰራ መቆቱን አንስተዋል። የሀገሪቱን ሀብት በሚገባ ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት በሳይበር ላይ የሚደረጉ ወንጀሎችን ለመከላከል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የገቢዎች ሚንስቴር ሚኒስተር ድኤታ ተስፋዬ ቱሉ በበኩላቸው የገቢዎች የታክስ ስርአት ማዘመን ወንጀል መከላከል እና ዋና ዋና ስራዎችን በቴክኖሎጂ እየከወነ በመሆኑ መረጃዎችን ከሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ ብሎም ለመከላከል እርስ በእርስ የሚደረገውን የመረጃ ልውውጥ ደህንነቱን ለማረጋገጥ በጋራ መስራቱ ውጤት እንደሚያመጣ ገልፀዋል።

በተያያዘም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እና የፍትህ ቢሮ የሀብት አሰባሰብን በተመለከተ እና ወንጀሎችን ለመከላከል በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።