አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Nested Applications

Asset Publisher

የቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። Thu, 18 Apr 2024

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅም ወደፊት የሚያሻግር ነው!

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅም ወደፊት የሚያሻግር ነው! Wed, 17 Apr 2024

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ 1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ 1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ Tue, 9 Apr 2024

ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጋራ ለምስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጋራ ለምስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ Thu, 4 Apr 2024

Asset Publisher

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡