አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Nested Applications

Asset Publisher

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ Wed, 13 Sep 2023

"ለውጥን የማፅናት ምዕራፍ" በሚል መሪ ቃል የ2016 አዲስ አመት መቀበያ ልዩ ፕሮግራም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተካሄደ

"ለውጥን የማፅናት ምዕራፍ" በሚል መሪ ቃል የ2016 አዲስ አመት መቀበያ ልዩ ፕሮግራም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተካሄደ Wed, 13 Sep 2023

ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ!!

ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ!! Wed, 13 Sep 2023

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2016 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2016 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ Wed, 13 Sep 2023

Asset Publisher

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡