ኢመደኤ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፡ መስከረም 26/2014፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ በአሸባሪዉ የትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ የአፋር ክልል ነዋሪዎች አጋርነቱን ለመግለፅ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

በድጋፍ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ይህ ድጋፍ በመላው የተቋሙ አመራርና አባላት ስም ሲያርጉ በደስታ መሆኑን ገልጸው ድጋፉ ለአፋር ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ-ልማቶች ወደነበሩበት ቦታ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ተቋማቸው የበኩሉን አጋርነት ለመግለጽ ነዉ ብለዋል።

ኤጀንሲዉ በተሰጠው ተልዕኮ ከሚያደርገዉ ቴክኒካል ድጋፍ በተጨማሪ በአሸባሪዉ የትህነግ ቡድን በአፋር ክልል ለወደሙ መሰረተ-ለማቶች አና ከቀያቸዉ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች አጋርነቱን ለመግለጽ እና ከጎናቸው መሆንን ለማሳየት የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል ሲሉ ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የኤጀንሲዉ አባል ሆነዉ የመዝመት ጥያቄ ላቀረቡ አባላትም አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ መላካቸውን በድጋፍ ረክክቡ ወቅት ገልጸዋል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ በበኩላቸዉ በወራሪዎች ግፍ የተነሳ ስቃይ እና እንግልት እየደርሰበት ለሚገኘው ህዝባቸው ኤጀንሲዉ ድጋፍ በማድረጉ በአፋር ክልል ህዝብ፣ በክልሉ መንግስት እና በተፈናቃዮቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በአሁኑ ሰዓት 200 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በአፋር ክልል ብቻ ከቀያቸው መፈናቀላቸዉን የገለጹት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በኢመደኤ የተደረገው ድጋፍ ተፈናቃዮቹን ወደነበሩበት ቀዬና አኗኗር ለመመለስ የራሱን አሰተዋጽኦ ያበረክታል ብልዋል።

"የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በክፉ ቀን የደረሱልን በመሆኑ መቼም አንረሳቸሁም፤ ሁሌም እናስታውሰዋለን" በማለት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አወል የገለጹ ሲሆን ወደፊትም ከኢጀንሲዉ ጋር በቴክኖሎጂ ሽግግር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኤጀንሲዉ አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ለመከላከያ ሠራዊት ደጋፍ ከማድረጋቸውም ባሻገር ደም የለገሱ ሲሆን በትላንትናዉ ዕለትም ተቋሙ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ መደረጉ ይታወሳል።