ድሮን አምርቶ እስከ መታጠቅ
ድሮን አምርቶ እስከ መታጠቅ
ከዚህ ቀደም ድሮን መታጠቅ ቀርቶ ገዝቶ ለመጠቀም እጅግ ከባድ ነበር፤ ዛሬ ላይ ይህ ሁሉ አልፎ በራስ አቅም እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያሉ ተቋማት ለተለያዩ ዓላማ የሚዉሉ ድሮኖችን እያመረቱ እንደሚገኙ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እያመረተቻቸው የሚገኙ ድሮኖች የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ማድረግ እንደሚያስችሉ ያነሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂዎችን ከመግዛት አልፋ ማምረት መጀመሯ በዘርፉ አስደናቂና ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስመዘገበች መሆኑን ማሳያ ነዉ ብለዋል።