ጥቅምት 24 ቀን፣ 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አንረሳውም!!

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ እና የሰላም ሚንስቴር አመራርና ሠራተኞች "አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ!" በማለት አምና ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜኑ ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በጋራ አስበዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ቀኑ እንቁ የሆነችውን ሀገራችንን በሚጠብቁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ ክህደት የምናስብበት ቀን ነው ብለዋል፡፡

ከክህደት ሁሉ ትልቁ ክህደት የተሸከመን ትከሻ መውጋት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የተፈጸመውን ጥቃት ያጎረሰን እጅ፣ ያጠባን ጡት እንደመንከስ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም መስዕዋት የሆኑ የሠራዊቱ አባላትን ሁልጊዜም እናስታውሳቸዋለን ያሉ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውንም እየደገፍን፣ ለተጎዱትና ለቆሰሉት አባላት ደግሞ ደማችንን እየሠጠን ዛሬም ከሠራዊቱ ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲሉ ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንድኣ በበኩላቸው ጥቃቱ የተፈጸመው በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት ላይም ነበር ብለዋል፡፡

ለሀገራችን መከታ፣ ጠበቃና መለያ በመሆን መስዕዋት የሆኑትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትንም ዘወትር እያሰብን እንኖራለን ሲሉ አቶ ታዬ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ በዱር በገደሉ ለሚዋደቁ የሀገር መከላከያ የሰራዊት አባላት ድጋፍ ማድረግ፤ እያንዳንዳችን በተሠማራንበት የሙያ ዘርፍ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣትና ለደህንነታችን እና ለሰላማችን ዘብ መቆም ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉም አቶ ታዬ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት አመራርና ሠራተኞችም ለ45 ሰከንዶች የቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ በማድረግና ጧፍ በማብራት አምና ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰው የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አስበዋል፡፡