በሶማሊያ የመረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ኃላፊ የተመራ ልዑክ በኢመደአ ጉብኝት አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀነራል ማሀድ ሞሐመድ የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎበኘ፡፡

ከፍተኛ ልዑኩ በኢመደአ በነበረው ጉብኝት የኢንፎርሜሽን እና ኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ደህንነት በማረጋገጥ በኩል በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ሥራዎችን እንዲሁም የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ተመልክቷል፡፡

ልዑካን ቡድኑ ኢመደአ ከውጭ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በመላቀቅ ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ በኩል ሰፋፊ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ በቀጣይም ቀጠናዊ የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡  

የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች፣ በአቅም ግንባታ መስኮች እንዲሁም ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ የጋራ ስምሪቶች ዙሪያ የተለያዩ ምክክሮችን እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

ሶማሊያ የመረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በትላንትናው እለት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል፡፡