ኢመደአ እና ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ አበባን ከተማ ስማርት ለማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ስምምነት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና ለማዘመን "አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ" ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋራ በጋራ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል፡፡

ይህ ስራ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመንና ከተማዋን ስማርት በማድረግ የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስ ነው። በተለይም ከተማዋ ያላትን አለም አቀፍ ደረጃ የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችላት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡