ኢመደኤ በማህበራዊ አገልግሎት ያደሳቸውን መኖሪያ ቤቶች አጠናቆ ለነዋሪዎች አስረከበ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ በክረምት ማህበራዊ በጎ አገልግሎት ያደሳቸውን ሁለት የአረጋዊያን መኖሪያ ቤቶች ዕደሳ አጠናቆ ለነዋሪዎች ዛሬ አስረክቧል፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተካሄደው የርክክብ ስነ-ስርዓት የተገኙት የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ ጳጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም ኢመደኤ የስጀመራቸውን የመኖሪያ ቤቶች ዕደሳ ግንባታ አጠናቆ በዛሬው ዕለት ለነዋሪዎቹ ለማስረከብ በመብቃቱ ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

 

ተነሳሽነት እና ቀና አስተሳሰብ ካለ ብዙ መልካም ነገሮች መስራት ቀላል መሆኑን ያወሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም ኢመደኤ ከክፍለ ከተማውና ከወረዳው ጋር በመነጋገር የተለያዩ ማህበራዊ የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፎዚያ መሐመድ በበኩላቸው እንዲህ ዓይነት ሰብዓዊነት የተሞላው መልካም ሥራ ተሠርቶ በማየታቸው ልባዊ የሆነ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

"ክፉ ቀን ገጥሞን አንዳችን ሌላውን በማገዝ መሻገር እንደምንችል የሚያሳይ በጎ ተግባር ነው" ያሉት ወ/ሮ ፎዚያ የህዝባችንን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት እየሠራን የሀገራችን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም በዚህ በጎ ተግባር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለተወጣው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ሌሎች አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

መኖሪያ ቤታቸው የታደሰላቸው ወ/ሮ አሰገደች መለሰ ጠዋሪ ደጋፊ እንደሌላቸው እና አቅመ ደካማ መሆናቸውን ተመልክተው መኖሪያ ቤታቸውን እንዲታደስ ያደረጉላቸውን አካላትን አመስግነዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ኤጀንሲው በማህበራዊ አገልግሎት ላበረከተው አስተዋፅኦ የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷል፡፡

ለሁለቱ ቤቶች ዕድሳት በአጠቃላይ 1.5 ሚሊዮን ገደማ ወጪ የተደረገ ሲሆን ቤቶቹን ገንብቶ ከማጠናቀቅ ባለፈ የቤት እቃዎች እንዲሟሉ መደረጉን በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል።