የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና አሪፍፔይ የዲጂታል ክፍያ ስርአት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) እና አሪፍፔይ የዲጂታል ክፍያ ስርአት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬዉ ዕለት ተፈራርመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት በኢመደኤ የደራሽ የዲጂታል ክፍያ ፕላትፎርም ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ገብረየስ ኤጀንሲዉ ህብረተሰቡን ይጠቅማሉ ባላቸዉ ጉዳዮች ከመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሚሠራ ገልጸው ከአሪፍፔይ ጋር የተደረሰዉ ስምምነትም አንዱ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

በስምምነቱ ላይ የተገኙት የአሪፍፔይ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃብታሙ ታደሰ በበኩላቸዉ ኩባንያቸዉ ከደራሽ ፕላትፎርም ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ከዘጠና ከመቶ በላይ ግብይት እየተደረገበት ያለዉን የጥሬ ገንዘብ ልዉዉጥ ጥገኝንትን ከመቀነስ ባሻገር ደንበኞች ከተለያዩ ተቋማት ላገኙት አገልግሎት ክፍያዎችን በተቀላጠፈና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በቀላሉ ለመክፈል ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ስለ ኩባንያቸዉ ጥቅም እና ድርሻ ባደረጉት ገለጻ “አሪፍፔይ” “ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂ መሆኑን እና አንድ ተጠቃሚ አካዉንቱን ከአሪፍፔይ መተግበሪያ ጋር ሊንክ በማድረግ ባለበት ቦታ ሆኖ የውኃ፤ መብራት፤ የትምህርት፤ የታክሲ፤ የሱፐር ማርኬትና ሌሎች የግብይት አገልግሎቶችን ለመፈጸም የሚያስችል ነዉ” ብለዋል።

ደራሽ የዲጂታ ክፍያ ፕላትፎርም ወደ ስራ ከገባ በኋል 50 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልዉዉጥ የተደረግ ሲሆን ከ16 ባንኮች ከ10 ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።