የኢመደአ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ ዐሻራቸዉን አሳረፉ
የኢመደአ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ ዐሻራቸዉን አሳረፉ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) አመራሮችና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ አካል በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ።
በመርሃ ግብሩ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድን ጨምሮ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ኢመደአ እንደ ተቋም ከተሰጠዉ ሃላፊነት ባሻገር ሀገራዊ ሚናቸዉ ከፍ ባሉና ትዉልድ ተሻጋሪ ስራዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት 6 አመታት በተካሄዱ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ላይ ከመሳተፍ ባሻገር፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
በዚህም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ባለዉ 7ኛው ዙር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን በመትከል የዘመቻዉ አካል በመሆን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ላይ አሻራቸዉን አሳርፈዋል።