"ያለንን አቅም አሰባስበን የሀገራችንን የሳይበር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ይገባል" የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ "የዲያስፖራዉ ተሳትፎ፣ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት" በሚል መርህ የምክክር መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

በመርሃ ግብሩ የዲያስፖራዉ ማህበረሰብ ከኤጀንሲዉ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በምክክር መድረኩ የኤጅንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ባስተላለፉት መልዕክት የእናት ሀገራችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እንዲሆን የራሳችሁን አስተዋጽኦ ለማበርከት በመምጣታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

 

በዚሁ ወቅት በውጪም ይሁን በዉስጥም ያለንን አቅም እና እዉቀት አሰባስበን የኢትዮጵያን የሳይበር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ለሚደረገዉ ሩጫ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ተሳትፎ በጣም ጠቃሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራችን ዘግይቶ ወደ ቴክኖሎጂው የመግባት ጥቅም /Late comer Advantage/ በትክክል መጠቀም እንድትችል የዳያስፖራዉ ሚና ከፍ ያለ ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያን ማንም የማይጠመዝዛት ሀገር ለማድረግ በጋራ መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን ብለዋል።

ኤጀንሲዉ ከዲያስፖራዉ ማህበረሰብ ጋር ባደረገው ዉይይት በዘርፉ ያሉትን የሰዉ ሃይል ክፍተት ለመሙላት ሊደረጉ ስለሚገቡ ጉዳዮች፣ ከግል ተቋማት ጋር ሊኖር ስለሚገባ የጎንዮሽ ትብብር እንዲሁም ወደፊት ኤጀንሲዉ ከዲያስፖራዉ ጋር በምን መልኩ በጋራ መስራት እንደሚገባ እና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።

የዲያስፖራዉ ማህበረሰብ በኤጀንሲው የተሰሩ የተለያዩ ስራዎችን፣ የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የታለንት ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡