ኢመደኤ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ በኤጀንሲው ለተመዘገቡ የመገናኛ ኮሙዩኒዩኬሽን መሣሪያዎች የማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሊሰጥ ነዉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

 በቅርቡ ኤጀንሲው ለመዘገባቸው የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች የባለቤትነት ማርጋግጫ ሰርተፍኬት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።

ኢመደኤ በተሰጠዉ ሥልጣን እና ኃላፊነት መሰረት በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን መጠን እና ዓይነት ለማወቅ ከዚህ ቀደም ምዝገባ ማድረጉ ይታወቃል።

በዚህም በወቅቱ ከ25ሺ በላይ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን ኤጀንሲዉ መመዝገብ መቻሉን በኤጀንሲዉ የቴክኖሎጂ እቃዎች ክትትል እና ዉል ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ተመስገን አስማረ ተናግረዋል።

የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች በዓይነት እና በመጠን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም በህጋዊ መንገድ ለተመዘገቡ መሣሪያዎች ኮድ በመስጠት ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ የሀገር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ እንደሚያግዝ አቶ ተመሰገን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኤጀንሲው የባለቤትነት ማርጋግጫ ሰርተፍኬት መስጠቱ በድብቅ ወደ ሀገር ዉስጥ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን በማስገባት በሚጠቀሙ ህገወጥ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚያስችለዉም ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለሚያከናውነው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የመስጠት መርሃግብር እና ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ ማስታወቂያ የሚያወጣ ይሆናል፡፡