ኢመደአ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፡ የካቲት 15/2014፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /ኢመደአ/ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው አበይት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች እና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

 

በውይይታቸውም ሁለቱ ተቋማት በትብብርና በቅንጅት ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች በተለይም ከህግ ማዕቀፍ፣ ከተልዕኮ፣ ከሰው ሀብት ማልማት፣ ከቴክኖሎጂ፣ ከሀብት አጠቃቀም እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም እንደዚህ አይነት የውይይት መድረክ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ያሉት አመራሮቹ በጋራ መስራታቸው የሀገርን ሀብት ከብክነት መጠበቅ ይስቻላል ብለዋል፡፡

ሌሎች ተቋማትም እንደሀገር በትብብርና በቅንጅት ተናበው መስራት ቢችሉ ሀገሪቷን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ ይቻል ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

ከውይይቱ ጎን ለጎን የአስተዳደሩን የሳይበር ተሰጥዖ ልማት ማዕከልን፣ በአስተዳደሩ ለምተዉ በዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል የቀረቡ ምርት እና አገልግሎቶችን እንዲሁም የኢመደአ ሠራተኞችና የኃላፊዎችን ቢሮዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ኢመደአ እየሠራ ያለው ሥራ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡