አስተዳደሩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ግለሰቦች እንደሚደግፍ እና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው የሳይበርና ተያያዥነት ያላቸው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሠራ ገለጸ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ፡ የካቲት 21/2014፡- የኢንፎርሚሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን /ኢመደአ/ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ግለሰቦች እንደሚደግፍ እና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው የሳይበርና ተያያዥነት ያላቸው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሠራ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሹመቴ ይህን ያሉት በቅርቡ በግሉ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን የሰራዉን ወጣት አማኑኤል ባልቻ እና የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኢመደአን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡

በዚሁ ወቅት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው አስተዳደሩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ግለሰቦች እንደሚደግፍ እና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው በሳይበርና ተያያዥነት ባላቸው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሠሩ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

በግሉ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን በመስራት ውጤታማ የፈጠራ ሥራ ያበረከተውን የደምቢ ዶሎ የዩኒቨርሲቲ መምህር ወጣት አማኑኤል ባልቻንም አስተዳደሩ በሰዉ ኃይል እና በማቴሪያል በመደገፍ ዓላማዎቹ እንዲሳኩ እና ሀገራችንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን እንድትችል የድርሻውን እንደሚወጣ ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠውላቸዋል።

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ተሰጥኦ ያላቸዉን ታዳጊዎችን በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ የተሰጥዎ ማዕከል እያበቃ እንደሚገኝ ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ እንደ አማኑኤል ያሉ የፈጠራ ባለቤቶችም በአስተዳደሩ ዉስጥ ያሉትን አቅሞች መጠቀም እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን አስተዳደሩ የሰዉ ሃይል እና አቅም እንዳይበታተን በሳይበር ምህዳሩ ዉስጥ ተጽእኖ ያላቸዉን አካላት በማሰባሰብ አቅምን በማስተባበር ስራዎችን ይሰራል ብለዋል።

በዚሁ ጉብኝት ላይ የተገኙት የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ በበኩላቸዉ አስተዳደሩ ይህን እድል መፍጠሩን አመስግነዉ በዩኒቨርሲቲዉ ያሉ እና ተሰጥኦ ያላቸዉን ሌሎች ተማሪዎችንም በማሰባሰብ በጋራ የምንሰራበት አማራጮችን እንፈጥራለን ብለዋል።

በቀጣይም የተለያዩ እቅዶች እንዳሉት የጠቆመዉ የፈጠራ ባለቤቱ እና የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አቶ አማኑኤል ባልቻ በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን ውስን መንገደኞችን የመያዝ አቅም ያለው የራሱን ሰዉ አልባ አውሮፕላን የመስራት እቅድ እንዳለዉም ጠቁሟል።

ወደፊት ሊያሳካቸዉ ላሰባቸው አላማዎች አስተዳደሩ የሚያደርግለት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ድጋፍ እንዲደረግለት ለተቋሙ ጥሪ አቅርቧል።

የኢንፎርሚሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች በሳይበር ደህንነት ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎችን በሳይበር ተሰጥኦ ልማት ማዕከል አቅማቸው እንዲጎለብት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በዘርፉ የሚያደርገውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡