የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለሁሉ አቀፍ እና አካታች ልማት በሚል ርእስ ኮንፈረንስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2014: የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለሁሉ አቀፍ እና አካታች ልማት በሚል ርእስ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ እና አዉደ ጥናት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነዉ።

በዚህ ኮንፈረንስ እና አዉደ ጥናት ላይ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ የመክፈቻ ንግግራቸውን ለኢትዮጵያ አንድነት በማይደራደሩት እና በጀግኖች ሃገር በጎንደር ተገኝቼ ንግግር እንዳደርግ እድሉን ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ብለው ጀምረዋል።

ጊዜዉ በዲጂታል ምህዳሩ ላይ በጋራ ልንሰራበት የሚገባ ነዉ ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ አስተዳደሩ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከሚሰሩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት በሩ ክፍት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሃገሪቱ ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የሳይበር ደህንነት ጉዳይን የዋና ስራቸዉ አካል አድርገዉ በመዉሰድ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ ትምህርት ቤቶች ተሰጥኦ ያላቸዉን ታዳጊዎች በመመልመል ለዘርፉ ማደግ የበኩላቸዉን ስራ ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን በበኩላቸው የዲጂታል ምህዳሩ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያየ መልኩ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነዉ ብለዋል። የዲጂታል አማራጮችም የኮቪድ-19 መከሰትን ተከተሎ ዋና የቀዉስ መቀነሻ በመሆን ከፍተኛ ፋይዳ መጫወት መቻላቸውን ገልጸዋል።

የዲጂታል ምህዳሩን በመጠቀም በሃገራችን ላይ የተሰነዘረዉን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለመከላከል የዲጂታል አማራጭ የሆኑትን የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም ከህግ ማስከበር እና የህልዉና ዘመቻዉን ለመመከት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት መቻሉንም አያይዘው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዉ የዲጂታል ምህዳሩን መልካም እድል ለመጠቀም ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጀምሮ በታዳጊዎች ላይ የተለያየ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራ መሆኑን የገለጹት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ይህም በዘርፉ ፍላጎት እና አቅም ያላቸዉን ታዳጊዎችን በመለየት እና አቅማቸዉን በማሳደግ ሃገሪቱ ያላትን የሰለጠነ የሰዉ ሃይል ክፍተት ይሞላል ብለዋል።

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፉም ሆነ እንደ አጠቃላይ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ በልዩ ሁኔታ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ስራዎችን በትብብር እንደሚሰሩም ዶ/ር አስራት ገልጸዋል።