ኢመደአ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከሶስት ባንኮች ጋር ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ካሉበት ቦታ ሆነው እንዲከፍሉ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

 በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ካሉበት ቦታ ሆነው እንዲከፍሉ ለማስቻል "ደራሽ የተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም" መተግበሪያን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የተካሄደው የጋራ ስምምነት ለባንኮች የተሳለጠ አሰራር እንደሚዘረጋ አስታውሰው በፋይናንስ ሰርዓቱ ውስጥ የኢ-ፔይመንት የገቢ አሰባሰቡን እንደሚያዘምነው አመላክተዋል ፡፡ ለዚህም አስተዳደሩ ግብር ከፋዮች ማንኛውንም አገልግሎት ካሉበት ቦታ ሆነው እንዲጠቀሙደራሽየተሰኘ መተግበሪያ አልምቶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ሚኒስትር ዴኤታ / መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው ባንኮች በግብር አሰባሰቡ የኢ-ፔይመንት አሰራሩ የታክስ አሰባሰቡን እንደሚያቀላጥፈው ገልጸው ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሸጋገሩ ለግብር ከፋዩ የበለጠ እንደሚያግዘው አስረድተዋል ፡፡

በጋራ ስምምነቱ የተካተቱት ባንኮች፤  እናት ባንክ፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ እና ቡና ባንክ ሲሆኑ ግብር ከፋዩ በተጠቀሱት ባንኮች አማካኝነት  -ፔይመንት አሰራሩን በዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላል ፡፡

ደራሽየተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም በኢመደአ ለምቶ ወደስራ የገባ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የገቢዎች ሚኒስቴርን ጨምሮ ለተለያዩ ባንኮች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ተደራሽ በመሆን ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ ክፍያዎቻቸውን በቀላሉ ለመፈጸም የሚያስችላቸው የክፍያ ፕላትፎርም ነዉ።