በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነትና ሌሎችም ተቋማት የጋራ ጥረት እየተመከተ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]



 በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነትና ሌሎችም ተቋማት የጋራ ጥረት እየተመከተ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት (ኢዜአ) ጋር ቆይታ ያደረጉት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የመረጃ ጦርነት በመመከት ረገድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትን አስተዳደር እና ሌሎች የመረጃ ደህንነት ተቋማት በቅንጅት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ የተከፈተባትን የተቀናጀ ግራጫ ጦርነት እየተፋለመች መሆኗን መግለፃቸው ይታወሳል።

ግራጫ ጦርነቱ የሳይበር ጥቃትን፣ ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻና የመረጃ ጦርነት፣ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እና ባንዳዎችን በመጠቀም ህዝብን መከፋፈልና ማጋጨትን ጭምር ያካተተ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም መንግሥት ጦርነቱን ለመመከትና ህግ ለማስከበር እየሞከረ መሆኑን ጠቅሰው፤ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ትክክለኛ ፈጣን መረጃን ወደ ህዝብ በማድረስ የመረጃ ጦርነቱን ለመመከት ስልት መነደፉን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች በሀሰተኛ መረጃ ህዝቡን ለመከፋፈል የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው የመረጃ ጦርነቱ አገር ለማፍረስ ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት በተቀናጀ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን አብራርተዋል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነት ተቋማትና ሌሎችም የጋራ ጥረት እየተመከተ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።

መንግሥት የጠላትን የመረጃ ጦርነት ለመመከት ተቋማትን በማጠናከር ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመረጃ ትክክለኛነትን ማጣራት፣ ወደ ህዝብ ፈጣን መረጃን ማድረስና አጀንዳ መቅረፅ ላይ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑንም አንስተዋል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ትክክለኛውን መረጃ አጣርቶ ለህዝብ በማድረስ የመረጃ ጦርነቱን ለመመከት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል።

የመረጃ ጦርነቱን በመመከት ሂደት የመገናኛ ብዙሃንም የድርሻቸውን እንዲወጡ ሚኒስትር ዴታዋ አስገንዝበዋል።

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት - ኢዜአ