ኢትዮጵያ በታሪክ ፈጣሪን ከመፍራት፣ ከማክበር እና ከማመስገን ጋር የተቆራኘች ናት - ሹመቴ ግዛው (ደ/ር) የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ ታመስግን በሚል መርሃ ግብር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የሰላም ሚንስቴር፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራር እና ሰራተኞች በጋራ አክብረዋል፡፡

ሹመቴ ግዛው (/) በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በታሪኳ ፈጣሪን ከመፍራት፣ ከማክበር እና ከማመስገን ወደኋላ ያለቸበት ጊዜ እንደሌለ በመጥቀስ ተባብረን ስንሰራ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፤ ለዚህም ጀግኖች አትሌቶቻችን በአሜሪካ ኦሪጎን የዓለም ሻምፒዮና ያስመዘገቡት አኩሪ ድል ሕያው ምስክር ነው ብለዋል፡፡ ሁላችንም በየግላችን ፈጣሪን እናመሰግናለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደ ሃገር እና እንደ ሕዝብ በጋራ በመሆን ስለተደረገልን ነገር ሁሉ ማመስገን ይገባል ብለዋል፡፡   

የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ታመሰግናለች የሚለው መርሃ ግብር በዋናነት አንድነትን ለማጉላት የታለመ እንደሆነ በማሰብ ለአንድነት የተከፈለውን ዋጋ እና በአንድነት ያሳለፍናቸውን ፈተናዎች የምናስብበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በተናጠል ከምናደርገው ጉዞ በላይ ተባብረን ስንሰራ ውጤታማ እንደምንሆን እያሰብን በትብብራችንም መመሰጋገን አለብን ብለዋል፡፡

ታዬ ግርማ (/) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በአንድነት ውስጥ መስጠት እና መሰጠትን ከግምት በማስገባት መመሰጋገን አለብን፤ እርስ በእርሳችን ስንመሰጋገን ፈጣሪም ይረዳናል ብለዋል፡፡

በምስጋና ፕሮግራሙ የአራቱም ተቋማት አመራርና አባላት እለቱን በማስመልከት ኢትዮጵያን ከተለያዩ መከራዎች ጠብቆ ላቆያት ፈጣሪ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡