ችግኝ ስንተክል ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን፣ መተሳሰባችንን እና ፍቅራችንን እያሰብን ነው - ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራር እና አባላት በአይ.. (ICT) ፓርክ "አሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መርሃ ግብር ከሁለት አምስት መቶ (2,500) በላይ የፍራፍሬና የዛፍ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (/) በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ እለት ችግኝ ብቻ ሳይሆን ፍቅርን፣ ሰላምን፣ አንድነትንና የጎደሉንን መልካም ነገሮች ሁሉ መትከል፣ መንከባከ እና ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ሀገር እና መጪው ትውልድ ችግኝን ብቻ ሳይሆን ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትን እና መልካም ነገሮችን ተክለን ለትውልድ እንድናስተላልፍ ይጠብቅብናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ችግኝ የምንተክለው ዛፍ ስለሌለን፣ ተራሮቻችን ስለተራቆቱ ብሎም የኢኮኖሚያችን መሰረት የሆነው መሬታችን በመሸርሸሩ ነው፡፡ ይህንን ጉድለት ለመሙላት ችግኝ እንደተከልን ሁሉ ፍቅር፣ አንድነትን ሰላምን እና መከባበርን በሀገራችን እንድንተክል፣ እንድንከባከብና እንድናሳድግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በየአመቱ የክረምት ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማካሄድ ባለፈ የተተከሉ ችግኞችን በበጋ ወቅትም የሚንከባከብ ሲሆን፤ በእለቱም በተቋም ደረጃ 2012 እና 2013 የተተከሉ ችግኞች የደረሱበትን ደረጃ ጉብኝት ተደርጓል።

ዋና ዳይሬክተሩ / ሹመቴ ግዛው በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ በቀጣይም የተራቆተ ስፍራ ለማልማት ከመንግስት እና ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በባለቤትነት አረንጓዴ ለማልበስ እና በዘላቂነት ለመንከባከብ በእቅድ እንደተያዘ ገልጸዋል፡፡