ኢመደአ እና አዋሽ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው እና የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጸሃይ ሽፈራው ፈርመውታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኢመደአ የአገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ ለሚያከናውናቸው ሁለንተናዊ ሥራዎች የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የተደረገ ሲሆን፤ በሌላም በኩል የባንኩን የኢንፎርሜሽንና ኢንፎርሜሽን መሰረት ልማት ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ድጋፍና እገዛ በኢመደአ በኩል ይሰጣል፡፡

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት ጠንካራ ሃገር መገንባት የሚቻለው ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡ ኢመደአ የአገራችንን የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ዋና ተልዕኮውን ለማሳካት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ይሰራል ያሉት ዶ/ር ሹመቴ፤ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር የተደረገው ያጋራ የመግባቢያ ስምምነት ፊርማም የአስተዳደሩ የትብብርና የቅንጅት ሥራ አንዱ አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጸሃይ ሽፈራው በበኩላቸው ኢመደአ የፋይናንስ ሴክተሩን ጨምሮ ቁልፍ የሃገራችንን ተቋማት የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰራቸው ሥራዎች ከፍተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህንን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ ለኢመደአ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም የሁለቱ ተቋማት የትብብርና የቅንጅት ሥራ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡