የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን ኢመደአን ጎበኘ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን የደኅንነትና ሲቪል ሹማምንት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን  የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና መ/ቤትን ጎበኘ፡፡ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው የልዑካን ቡድኑ ነሃሴ 10/2014 ዓ/ም በኢመደአ ዋና መ/ቤት በመገኘት የአስተዳደሩን የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል፣ ዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴዎች ተመልክቷል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጉብኝትን ጨምሮ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታን በማረጋገጥና ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶች እንደሚፈጽም ይጠበቃል፡፡