የመጀመሪያው የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር / ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ / ባይሳ በዳዳ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ደረጄ እንግዳ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር / ሙፈሪያት ካሚል  በመረሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለአሁኑ ትውልድ የምትሆነዋን የነገዋን ኢትዮጵያን የምትገነቡት የዛሬ ታዳጊ ወጣቶች ናችሁ፤ ለዚህ ደግሞ መነሻችሁን ኢትዮጵያ መዳረሻችሁን አለም በማድረግ ያላችሁን እምቅ አቅም እና ችሎታ አውጥታችሁ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል።

አሁን ላይ በአለም መድረክ ከፊት የሚገኙት ሃገራት የእድገታቸው ሚስጥር በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሳይበር ኢንደስትሪ ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው በመስራታቸው በተለይም ደግሞ በዘርፉ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች ምቹ ሁኔታን መፍጠር በመቻላቸው ነው። በመሆኑም በዛሬው እለት በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ለዩ ተሰጥኦ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች የተዘጋጀው የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ አመላካች ነው ብለዋል።

አያይዘውም የፕሮግራሙ ተሳታፊ ታዳጊ ወጣቶች የሚሰሯቸው የፈጠራ ስራዎች ተጨባጭ የሃገራችንን ችገሮች የሚፈቱ፣ ለዜጎቻችን የስራ እድልን የሚፈጥሩ በአጠቃላይም የዲጂታል ኢንተርፕርነር ስነ ምህዳሩን የሚያሳልጡ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም የመጀመሪያውን የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ላዘጋጁት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም ይሄንን መልካም ጅማሮ በመደገፍ ረገድ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸዉ ኢመደአ ለሳይበር ታለንት ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በሃገራችን በሳይበር ደህንነት የሚገኙ ታለንቶችን ለማልማትና ለመጠቀም የሚያስችል ማዕከል አደራጅቶ ሥራውን በጀመረ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ 120 ሰልጣኞችን ተቀብሏል፡፡

ሆኖም ዘርፉ ከሚፈልገው የሰለጠነ የሰው ሃይል አንጻር በቂ ነው ለማለት አያስችልም፡፡ በመሆኑም የሳይበር ታለንትን የማልማት ጉዳይ የኢመደአ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ተቋማት በተለይም ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጀንዳ መሆን ይገባል ብለዋል ፡፡

ከዚህ አኳያ የኢመደአ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በዘርፉ ብቁ እና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ማፍራት እና ያለብንን የሙያተኛ እጥረት መቅረፍ የሚያስችል ሲሆን ሰልጣኞቹ ያላቸውን እምቅ ችሎታና ተሰጥዖ አውጥተው ያቀዷቸውን ፕሮጀክቶች እንዲያሳኩ ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ በማድረግም ጉልህ ሚናን ይጫወታል፡፡

ከዚህ በኋላ በሳይበር ደህንነት ላይ የሚደረጉ የታለንት ልማት ሥራዎች በተቋም ደረጃ ታጥሮ መቀመጥ ስለማይገባዉ በቀጣይ ሁሉምንም ዩኒቨርሲቲዎቻችንን ጨምሮ  ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር በትብብር እና በቅንጅት እንድንሰራ ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል ፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ / ባይሳ በዳዳ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን በያዘችው በሳይንስ፣ በኢኖቬሽን እና ፈጠራ ስራዎች ተልኮን እውን ማድረግ የሚቻለው የተቋማት ትስስርና ትብብርን በማጠናከር ብሎም በቁርጠኝነት ወደ ተግባር ማውረድ ሲቻል ነው ብለዋል ፡፡ 

በዘርፉ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ለመሆን ብቁ እና የፈጠራ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት  አቅም የሚጠይቅ፣ ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት ለመላቀቅ ሀገር በቀል እውቀቶችን በመጠቀም አስቻይ መሰረተ ልማቶችን እና የህግ መአቀፎችን ማዘጋጀት ብሎም በኢኖቬሽንና በፈጠራ የተገኙ ግኝቶች ወደ ሀብት እና የስራ እድል ወደሚሆኑበት ደረጃ ማሸጋገር ይጠይቃል፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከተለያዩ ከፍተኛ የትምርት ተቋማት ጋር የተጀመረው ትስስር እና ትብብር በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ አቅምን የሚፈጥር ነው፡፡ በዚህም ረገድ የኢኖቬሽንና  ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በተጀመሩት ትብብር እና ጥምረቶች የበኩሉን ሚና ለመጫወት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያው የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ  ላይ ተሳታፊ የሆኑ ሰልጣኖች ዕድሜያቸው 12 - 23 ሲሆኑ፤ በአጠቃላይም 60 ባለ ልዩ ተሰጣኦ ታዳጊ ወጣቶቾ በዚህ ሰመር ካምፕ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡