ለግል የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የተላለፈ ጥሪ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በየዓመቱ ጥቅምት ወር የሳይበር ደህንነት ወርን ያከብራል፡፡በመሆኑም አስተዳደሩ በ2015 ዓ/ም በሚያከብረዉ የሳይበር ደህንነት ወር ጀማሪ የግል ቴክኖሎጂ ተቋማት (start-ups) ፣ የሳይበር ደህንነት ብሎም ተያያዥነት ያላቸው የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት ባለቤት የሆኑ ድርጅቶች በአዉደ-ርዕይ መርሃ-ግብር ላይ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋዉቁ ከወዲሁ ለመጋበዝ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም፡-

  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ወይም የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ
  • የሚያቀርቡት የቴክኖሎጂ ምርት እና አገልግሎት አይነት የሚገልጽ ጽሁፍ
  • የተቋሙን ፕሮፋይል የያዘ ሰነድ
  • ለእይታ የሚቀርብ የቴክኖሎጂ ዉጤት ማቅረብ የምትችሉ ተቋማት

ነሃሴ 12/2014 ዓ/ም እስከ ነሃሴ 26/2014 ዓ/ም ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠየቁትን ማስረጃዎች በኢሜል አድራሻ ncsm3@insa.gov.et ላይ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማስታወሻ፡- በሳይበር ደህንነት ምርትና አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከፖሊሽድ ኤቨንትስ ጋር በመተባበር